facebookgoogle plustwitter

መኖር የሚቻል አልሆነም!!

መኖር የሚቻል አልሆነም!!

‹‹ራሷን ከመግደሏ በፊት የመጨረሻ ማስታወሻዋን ፦ ‹ሕይወት ሊኖሩት የሚቻል አልሆነም!! ይቅርታ አድርጉልኝ።› ብላ አሰፈረች።

መስጊድ . . ዩኒቨርሲቲ ነው

መስጊድ . . ዩኒቨርሲቲ ነው

‹‹መስጊዶች የእስላም ዩኒቨርሲቲዎች ነበሩ - አንዳንዶቹ ዛሬም ድረስ ናቸው። ዕውቀትን በተጠሙ ተማሪዎች የተጨናነቁ ነበሩ። እነዚህ ተማሪዎች፣ሊቃውንት በሃይማኖት፣በሕግ፣በፍልስፍና፣በሕክምና እና በሒሳብ ሳይንሶች ላይ የሚሰጡትን ሌክቸሮች ለማዳመጥ ይመጡ ነበር። ሊቃውንቶቹ ራሳቸው ዐረብኛ ይናገሩ ከነበሩ ከሁሉም የዓለም ክፍሎች የሚመጡ ነበሩ። ተማሪው ዜግነቱ የፈለገውን ቢሆን ሙሉ አቀባበል ይደረግለት ነበር።››

የአላህ ሥራ!!

የአላህ ሥራ!!

‹‹ቀደም ሲል ጥንታዊው የደቀልዲያኖስ ኢምፓይር ክፍል ተደርገው ይቆጠሩ በነበሩ አገሮች ውስጥ ስር በሰደደው የማሽቆልቆል ዘመን፣ከዐረቢያ በረሃዎች እምብርት አንዱድ ባለጋራ በድንገት ብቅ አለ። እርጅና የተጫጫነውን ያንን ኢምፓይር ማሳደድም ያዘ። በስተደቡብ አቆጥቁጠው ለነበሩ አዳዲስ ግዛቶችም ደመኛ ጠላት ሆነ። ይህ ባለጋራ ዓይን እያየ ጥንካሬና ግዝፈት መጨመሩን ቀጠለ። ፍጹምና ቅን የሆኑ፣የአላህ ቋሚ ረድኤት ወደ ጅሃድና ወደ አንጸባራቂ ድል የሚመራቸው ይመስል ነበር። ሶርያና ግብጽን በድል አድራጊነት መያዝም ተከተለ። በአጭር ጊዜ ውስጥም የሳሳኒያውያን ኢምፓይር ፈረካከሰ። የፍልስጥኤም አጋሮችም ያንኑ የሽንፈት ጽዋ ለመጎንጨት ተገደዱ።››

ይለያል . .

ይለያል . .

‹‹እንደ እስላም ከዐረባዊው ነቢይ የቀደሙትን ነቢያትና መልክተኞች የሚያከብር ሌላ ሃይማኖት የለም። ነቢያቱን ማክበርና በነርሱ ማመንን በምእመናኑ ላይ ግዴታ አድርጎ ይደነግጋል። በመተላለፍና በመገለጥ ከርሱ የቀደሙትን መለኮታዊ ሃይማኖቶችንም እንደ እስላም የሚያከብር ሌላ ሃይማኖት አይገኝም።››

የአምልኮተ አላህ (ዕባዳ) አጠቃላይ ግንዛቤ

የአምልኮተ አላህ (ዕባዳ) አጠቃላይ ግንዛቤ

ነብዩ  አንዲህ ብለዋል፦ ‹‹አንዳችሁ ችግኝ በእጁ እንደያዘ የትንሣኤ ቀን ቢደርስ ይትከለው (መትከሉን አይተወው)።›› [በአሕመድ የተዘገበ] የአላህ መልክተኛ ሆይ! አንዳችን የራሱን ሥጋዊ ፍላጎት አርክቶ በዚያ ምንዳ ያገኛልን?! ሲሏቸው፦ ፍላጎቱን በተከለከለ (ሐራም) መንገድ አርክቶ ቢሆን ኃጢአት ይሆንበት የለምን? በተመሳሳይ መልኩም በተፈቀደ (ሐላል) በመፈጸሙ ምንዳ ያገኝበታል።›› [በሙስሊም የተዘገበ]

አንብብ . . የእስላም ጥሪ

አንብብ . . የእስላም ጥሪ

‹‹እስላም - የሳይንስና የዕውቀት ሃይማኖት ነውና - ዕውቀት እንዲገበዩና የተማሩትንም ተግባራዊ እንዲያደርጉ ለተከታዮቹ ጥሪ የሚያደርግ መሆኑ ጥርጥር የለውም። የቅዱስ ቁርኣን የመጀመሪያው አንቀጽ ‹‹አንብብ በዚያ (ሁሉን) በፈጠረው ጌታህ ስም።›› የሚለው የአላህ (ሱ.ወ.) ቃል በመሆኑ ይህን ማድረጉም አስገራሚ አይደለም።››

ለምን አንሆንም?!

ለምን አንሆንም?!

‹‹እሰላም ይኸ ከሆነ፣ሁላችንም ሙስሊሞች ለምን አንሆንም?!››

ኦ አምላኬ!

ኦ አምላኬ!

‹‹የዘመናዊውን ስነፈለክ አንዳንድ ፎቶግራፎች ባየሁ ጊዜ የመጀመሪያ መስተጋብሬ ፦ ኦ አምላኬ! ሥራው ሙሉ በሙሉ ተሳክቷል፤በሞቴ እጹብ ድንቅ ነገር ነው ብዬ መጮኽ ነበር።››

ሃይማኖት ካልገራቸው የሰው አውሬዎች ናቸው!

ሃይማኖት ካልገራቸው የሰው አውሬዎች ናቸው!

‹‹አሜሪካ ትጸልያለች ወይስ አትጸልይም?›› በተሰኘ የዴቪድ ባርቶን መጽሐፍ ውስጥ በሰፈረውና በአንድ የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲ በተደረገ አኃዛዊ ጥናት መሰረት፦ - ከአሜሪካ ሴቶች መካከል 80% የሚሆኑት በሕይወታቸው ውስጥ ቢያንስ አንድ ጊዜ ለአስገድዶ መደፈር ጥቃት ተጋልጠዋል!! - በየዕለቱ ተገደው የሚደፈሩ ሴቶች ቁጥር ከ1900 በላይ ሲሆን፣በዚህም ምክንያት 30% ያህል የሚሆኑ አሜርካውያት ልጃገረዶች በአስራ አራት ዓመታቸው ለእርግዝና ለውርጃ ወይም ለወሊድ ይጋለጣሉ። - 61% የሚሆነው የአስገድዶ መድፈር ጥቃት የተፈጸመው ዕድሜያቸው ከአስራ ስምንት ዓመት በታች በሆኑት ሴቶች ላይ ነው። - 29% የሚሆነው የአስገድዶ መድፈር ጥቃት የተፈጸመው ከአስራ አራት ዓመት በታች በሆኑ ሕጻናት ላይ ነው።

ጠይቅ . . ቁርኣን መልስ ይሰጠሃል

ጠይቅ . . ቁርኣን መልስ ይሰጠሃል

‹‹ቁርኣን አጠናሁና ለሁሉም የሕይወት ጥያቄዎች መልሶችን አገኘሁበት።››